ልጥፎች

መሀረቤን ያያችሁ?

ምስል
መሀረቤን ያያችሁ? ዛሬ፡- እመት የቢጫወርቅ ከፊሉ ሳር ከፊሉ ቆርቆሮ በለበሰ ጣራ ስር፣በከፊል ከሲሚንቶና ከብሎኬት በከፊል በጭቃ ተዋቅሮ በግማሽ ቢጫ በግማሽ ጥቁር የተቀባ ግድግ ካቆመው ጎጆ አይሉት ቪላ ቤት ውስጥ፤ በግማሽ ከጠፈር በግማሽ ከሽቦ ተሰርቶ ግማሽ የሳር ግማሽ የስፖንጅ የሆነ ፍራሽ ከተካደመበት አልጋ ላይ፣ የፊታቸው ገጽታ በከፊል ፈግጎ በከፊል እንደጠለሸ፣ በቀኝ አይናቸው የተስፋ ብርሃን እየረጩና የግራ አይናቸው በበኩሉ በፍርሀት እንደተሞላ፣ ከፊል ሰውነታቸው ጤና ሆኖ ከፊሉ በደዌ እንደተመታ በመንቃትና በእንቅልፍ መሀል ሆነው በተንጋለሉበት በታከተው ሰው ድምጽ ደጋግመው ልጆቻቸውን ይማጸናሉ፡፡ ልጃቸው የእናቱ ልጅ ቆራሌ ወንድሞቹ በየመንደሩ “አሮጌ ቆርቆሮ ያለው” እያሉ ዞረው እየሰበሰቡ እቤት በሚከምሩት ቅራቅንቦ የተነሳ ያደፈውን የእናቱን መጎናጸፊያ ከብዙ ትርኪሚርኪዎች መሀከል ለመለየት ብቻውን ይታገላል፡፡ ልክ ሊያገኘው ሲል ልዋጭ ወንድሞቹ በበኩላቸው የእናታቸው የጥንት ግን ዝንተ-ዓለም አዲስ የሆነ መጎናጸፊያ አረጀ ብለው የነሱን አሮጌ አዲስ አስመስለው “ልማጭ ልዋጭ” እያሉ አዲሱን መጎናጸፊያቸውን በአሮጌ መሀረብ እየለወጡ አምጥተው ከቤት ያጠራቀመት የመሀረቦች ዲሪቶ ይናድና ሊገኝ ያለውን የእናቱን መጎናጸፊያ ይቀብርበታል፡፡ የእናቱ ልጅ ሳይታክት በብዙ ትግል ከብዙ ቅራቅንቦዎችና ዲሪቶዎች መሀል የእናቱን መጎናጸፊያ ዳግም ያገኘው ሲመስለውና በቀኝ እጁ ከፍ አርጎ ይዞ ለእናቱና ለወንድሞቹ ሊያሳያቸው ሲጣጣር ሌላ ያልታሰበ የመሀረቦች ቅራቅንቦና ዲሪቱ እንደገና ከየስርቻው እንደ አሸን እየፈሉ ተከምረው ይናዱበትና የእናቱን መጎናጸፊያ፣ እናትና ወንድሞቹን ይከልሉታል፡፡ የእናቱ ልጅ ተስፋ ሳይቆርጥ እንደምንም ተፍጨርጭሮ ከማህ...

.....አዲስ ዓመት የለም

.....አዲስ ዓመት የለም፡፡ ተፈጥሮ በፈጣሪዋ የተደነገገላትን ህግጋት አክብራ ጨረቃ በመሬት መሬት ደግሞ በፀሀይ ዙሪያ የሚያደርጉትን የማያባራ ኡደት ሲፈጽሙ እኛ በበኩላችን መዓልቱን በፀሀይ ሌቱን በጨረቃ አስልተን ለቀናቱ፣ ለወራቱና ለዓመታቱ ስያሜና ቁጥር እየሰጠን የዕለትና የዓመት ተግባራችንን አቅደን ወይም በዘፈቀደ እየፈጸምን በምድር የተሰጠንን የኑሮ ጊዜ እንገፋለን፡፡ ጊዜ በመስፈርታት ተሸንሽኖ ከ ሳድሲት ሃምሲት፣ ከራብዒት ሳልሲት፣ከካልዒት ኬክሮስ ከኬክሮስ ደግሞ ዕለታት እየተወለዱና ዕለታት አውደ ዕለትን፣ አውደ ወርህን፣ አውደ ዓመትን እየተኩ ና አውደ ዓመትም በበኩሉ ዓውደ አበቅቴ፣ዓውደ ፀሀይ፣አውደ ማሕተብ እየሆነ ግዙፉን ዓውደ ቀመርን ለመደረብ ጊዜ እንደ ወንዝ ወደፊት ብቻ ይፈሳል፡፡ ይህ የማያባራ የዘመን ዶፍ በተደጋገመ የመሬትና የጨረቃ ዙረት እራሱን ይደጋግማል፡፡ ምድርና ጨረቃ ኡደታቸውን ሲጨርሱ መልሰው ያንኑ ኡደታቸውን ይጀምሩና ከቅጽበት (ከካልዒት) ኬክሮስ ከኬክሮስ ዕለታት መልሰው እየተወለዱ ግዙፎቹ ዓዕዋዳት ዳግም ይወለዳሉ፤በዚህ ዙረት ውስጥ አዲስ ቁጥር እንጂ አዲስ ዕለት ወይም ዓመት የለም፡፡ በዘመን ጉዞ ላይ የሰው ልጅ አስተዋጾ ምንም ነው፡፡ በዚህ የጊዜ ፍሰት ውስጥ አዲሱ የሰው ልጅ አካልና መንፈስ ብቻ ነው፡፡ የአካል መታደስን በተመለከተ በየቀኑ 10-50 ትሪሊየን የሚደርሱ የሰውነታችን ሴሎች ሞተው በአዲስ እየተተኩ አዲስ አካላዊ ማንነት ያላብሱናል፡፡ ይህም ደግሞ የተፈጥሮ ህግ ስለሆነ በሰው ይታገዝ ይሆናል እንጂ አይገዛም፡፡ እናም ለሰው እውነተኛው አዲስ ነገር የመንፈስ አዲስነቱ ነው፡፡ የህይወቱ መነሻ የሆነውን የውስጥ ሀሳቡንና በመመርመር መረዳቱን ማስተካከል ወይም መቀየር፣ በመረዳቱ አመለካከቱን የመለወጥና...

ውኃ ይሰማል ጉድ በል አበሻ ውኃ ይሰማል አለች ፈረንጅ

ውኃ ይሰማል ጉድ በል አበሻ ውኃ ይሰማል አለች ፈረንጅ አሸናፊ አበራ ውድ የሸገር ታይምስ ቤተሰቦች እንደምን ሰንብታችኋል? የጥምቀትን በአልን በማሳበብ የጻፍኩትን ” ውኃ ና እግዜር” የሚለውን ጽሁፌን ስደመድም የውኃን ተአምራዊ ተፈጥሮ ለመንገር እንደምመለስ ቃል ገብቼ በነበረው መሰረት ባለቅኔው በአጼ ቴዎድሮስ የምናብ አንደበት ውስጥ “ቃል የእምነት እዳ ነው…”ያለውን አክብሬ እነሆ ተመለስኩ፡፡ ውኃ መሰረታዊ የፊዚክስንም ሆነ የኬሚስትሪን ህግ አይጠብቅም ለምሳሌ ሌሎች ቁሶች ሙቀት ሲነካቸው Heat cause expansion በሚለው የፊዚክስ ህግ መሰረት ሞሎኪውሎቻቸው ይስፋፋሉ ውኃ ግን በተቃራኒው ሙቀት ሲነካው ይኮማተራል ወይም (contract) ያደርጋል በቅዝቃዜ ጊዜ ደግሞ ይስፋፋል፡፡ ከቅዝቃዜ ነጥብ በታች ወይም below freezing point የሌሎች ቁሶች መጠናቸው (density) ሲቀንስ የውኃ ግን ይጨምራል above freezing point ሲሆን መጠኑ (density) ይጨምራል ከቅዝቃዜ ነጥብ በላይ ወይም above freezing point ሲሆን ደግሞ ይቀንሳል፡፡ ውኃ ብቻ የመሬት ስበትን እና ከባቢያዊ ግፊትን ጥሶ በረዣዥም ዛፎች ቅርፊት ውስጥ እያቆራረጠ ሽቅብ እስከ ጫፍ ይወጣል፤ውኃ ብቻ ሲፈልግ ፈሳሽ ሲሻው ጠጣርና ጋዝ በመሆን በተለያ ቅርጽ ይገኛል፡፡ ውኃ ከሌሎች ፈሳሶች በበለጠ ወደ ውስጡ የሚገቡትን ጠጣር ነገሮች በፍጥነት ያሟሟል ሌላም ሌላም፡፡ ውኃ ለምን የተለየ ሆነ የሚለውን ጥያቄ መመለስ የሚችለው እራሱ ውኃ ብቻ ይመስላል ጠያቂው ሳይንስ እንኳን መልሱን አልደረሰበትምና፡፡ የዚህ እንቆቅልሽ ፍቺ ሳይገኝ ተመራማሪዎችን በጥፍር ያቆመ ሌላ ክስተት በደቡብ ምስራክ ኤዠያ ውስጥ ተከሰተ፡፡ ጊዜው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ...