ልጥፎች

ከሴፕቴምበር, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

.....አዲስ ዓመት የለም

.....አዲስ ዓመት የለም፡፡ ተፈጥሮ በፈጣሪዋ የተደነገገላትን ህግጋት አክብራ ጨረቃ በመሬት መሬት ደግሞ በፀሀይ ዙሪያ የሚያደርጉትን የማያባራ ኡደት ሲፈጽሙ እኛ በበኩላችን መዓልቱን በፀሀይ ሌቱን በጨረቃ አስልተን ለቀናቱ፣ ለወራቱና ለዓመታቱ ስያሜና ቁጥር እየሰጠን የዕለትና የዓመት ተግባራችንን አቅደን ወይም በዘፈቀደ እየፈጸምን በምድር የተሰጠንን የኑሮ ጊዜ እንገፋለን፡፡ ጊዜ በመስፈርታት ተሸንሽኖ ከ ሳድሲት ሃምሲት፣ ከራብዒት ሳልሲት፣ከካልዒት ኬክሮስ ከኬክሮስ ደግሞ ዕለታት እየተወለዱና ዕለታት አውደ ዕለትን፣ አውደ ወርህን፣ አውደ ዓመትን እየተኩ ና አውደ ዓመትም በበኩሉ ዓውደ አበቅቴ፣ዓውደ ፀሀይ፣አውደ ማሕተብ እየሆነ ግዙፉን ዓውደ ቀመርን ለመደረብ ጊዜ እንደ ወንዝ ወደፊት ብቻ ይፈሳል፡፡ ይህ የማያባራ የዘመን ዶፍ በተደጋገመ የመሬትና የጨረቃ ዙረት እራሱን ይደጋግማል፡፡ ምድርና ጨረቃ ኡደታቸውን ሲጨርሱ መልሰው ያንኑ ኡደታቸውን ይጀምሩና ከቅጽበት (ከካልዒት) ኬክሮስ ከኬክሮስ ዕለታት መልሰው እየተወለዱ ግዙፎቹ ዓዕዋዳት ዳግም ይወለዳሉ፤በዚህ ዙረት ውስጥ አዲስ ቁጥር እንጂ አዲስ ዕለት ወይም ዓመት የለም፡፡ በዘመን ጉዞ ላይ የሰው ልጅ አስተዋጾ ምንም ነው፡፡ በዚህ የጊዜ ፍሰት ውስጥ አዲሱ የሰው ልጅ አካልና መንፈስ ብቻ ነው፡፡ የአካል መታደስን በተመለከተ በየቀኑ 10-50 ትሪሊየን የሚደርሱ የሰውነታችን ሴሎች ሞተው በአዲስ እየተተኩ አዲስ አካላዊ ማንነት ያላብሱናል፡፡ ይህም ደግሞ የተፈጥሮ ህግ ስለሆነ በሰው ይታገዝ ይሆናል እንጂ አይገዛም፡፡ እናም ለሰው እውነተኛው አዲስ ነገር የመንፈስ አዲስነቱ ነው፡፡ የህይወቱ መነሻ የሆነውን የውስጥ ሀሳቡንና በመመርመር መረዳቱን ማስተካከል ወይም መቀየር፣ በመረዳቱ አመለካከቱን የመለወጥና...

ውኃ ይሰማል ጉድ በል አበሻ ውኃ ይሰማል አለች ፈረንጅ

ውኃ ይሰማል ጉድ በል አበሻ ውኃ ይሰማል አለች ፈረንጅ አሸናፊ አበራ ውድ የሸገር ታይምስ ቤተሰቦች እንደምን ሰንብታችኋል? የጥምቀትን በአልን በማሳበብ የጻፍኩትን ” ውኃ ና እግዜር” የሚለውን ጽሁፌን ስደመድም የውኃን ተአምራዊ ተፈጥሮ ለመንገር እንደምመለስ ቃል ገብቼ በነበረው መሰረት ባለቅኔው በአጼ ቴዎድሮስ የምናብ አንደበት ውስጥ “ቃል የእምነት እዳ ነው…”ያለውን አክብሬ እነሆ ተመለስኩ፡፡ ውኃ መሰረታዊ የፊዚክስንም ሆነ የኬሚስትሪን ህግ አይጠብቅም ለምሳሌ ሌሎች ቁሶች ሙቀት ሲነካቸው Heat cause expansion በሚለው የፊዚክስ ህግ መሰረት ሞሎኪውሎቻቸው ይስፋፋሉ ውኃ ግን በተቃራኒው ሙቀት ሲነካው ይኮማተራል ወይም (contract) ያደርጋል በቅዝቃዜ ጊዜ ደግሞ ይስፋፋል፡፡ ከቅዝቃዜ ነጥብ በታች ወይም below freezing point የሌሎች ቁሶች መጠናቸው (density) ሲቀንስ የውኃ ግን ይጨምራል above freezing point ሲሆን መጠኑ (density) ይጨምራል ከቅዝቃዜ ነጥብ በላይ ወይም above freezing point ሲሆን ደግሞ ይቀንሳል፡፡ ውኃ ብቻ የመሬት ስበትን እና ከባቢያዊ ግፊትን ጥሶ በረዣዥም ዛፎች ቅርፊት ውስጥ እያቆራረጠ ሽቅብ እስከ ጫፍ ይወጣል፤ውኃ ብቻ ሲፈልግ ፈሳሽ ሲሻው ጠጣርና ጋዝ በመሆን በተለያ ቅርጽ ይገኛል፡፡ ውኃ ከሌሎች ፈሳሶች በበለጠ ወደ ውስጡ የሚገቡትን ጠጣር ነገሮች በፍጥነት ያሟሟል ሌላም ሌላም፡፡ ውኃ ለምን የተለየ ሆነ የሚለውን ጥያቄ መመለስ የሚችለው እራሱ ውኃ ብቻ ይመስላል ጠያቂው ሳይንስ እንኳን መልሱን አልደረሰበትምና፡፡ የዚህ እንቆቅልሽ ፍቺ ሳይገኝ ተመራማሪዎችን በጥፍር ያቆመ ሌላ ክስተት በደቡብ ምስራክ ኤዠያ ውስጥ ተከሰተ፡፡ ጊዜው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ...

ጥምቀት፣ እግዜርና ውኃ

ጥምቀት፣ እግዜርና ውኃ እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ፡፡ ጥምቀት የውኃ በአል ነው፡፡ በሌላ በኩል ጥምቀት ወይም ኤጲፋንያ   መገለጥ መታየት ማለት በመሆኑ ጥምቀት የመገለጥ ወይም አስተርእዮ በአል ነው፡፡ እንደ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ከህዳር 11 እስከ ህዳር17 ወይም እስከ ጾም ነነዌ ያለው ጊዜ የ አስተርእዮ (የመገለጥ) ጊዜ ይባላል፡፡ ሊቃውንቱ እንደሚናገሩት ዘመነ አስተርእዮ በሚባለው በ ዚህ ወቅት አምላክ ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡ፣ በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የአንድነትና የሦስትነት ምሥጢር መታወቁ፣ በቃና ዘገሊላ በተደረገው ሠርግ ላይ የመጀመሪያው ተዐምር በመፈጸሙ፣ አምላካዊ ኃይሉ መገለጡ እየታሰበ ምስጋና ይቀርባል። ከነዚህ ሶስት ዋና ዋና የመገለጥ ክስተቶች ሁለቱ ከውኃ ጋር የተገኛኑ ናቸው፡፡ ስለዚህ ስለውኃ የታወቁ ሳይንሳዊ እውነቶችን ከሀይማኖታዊ አስተምሮቶች ጋር በማቀኛጀት ለማውራት ከዚህ ወቅት የተሸለ ሌላ አጋጣሚ አላገኝም፡፡ *** በምድራችን ላይ ለቁጥር የሚታክቱ የተለያዩ የእምነት አስተምሮቶች ላይ የተመሰረቱ በርካታ ሀይማኖቶች አሉ፡፡ በሚገርም ሁኔታ እነዚህን ሀይማኖቶች የሚያግባባ አንድ ነገር ቢኖር ውኃ ብቻ ነው፡፡ እንደ ክርስትና እስልምና ሂንዱዚም ቡዲዝም ሺቶይዝ እና ሌሎቸም ታላላቅ ሀይማኖቶች ውኃን የሀይማኖታዊ ስርአቶቻቸው ማእከል አድርገው ይጠቀሙበታል፡፡ ይህ የጥምቀት በዓል በ ክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ት ተከታዮች ዘንድ የሚከበር በመሆኑ ኦርቶዶክሳዊ አስተምሮቶችን መሰረት አድርጌ   ሳይንሳዊ ግንቶችን እያጣቀስኩ ስለ ውኃ አወጋለሁ፡፡ *** መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚነግረን...