ትምህርተ ሃይማኖት አገናኝ አግኝ ፌስቡክ X Pinterest ኢሜይል ሌሎች መተግበሪያዎች ኦገስት 07, 2017 ትምህርተ ሃይማኖት ልብስ የሀፍረት መደበቂያ፣ የሀጢያት ካባ ነው ቢሉኝ፣ እርቃኔን መቆም ወደድኩኝ፡፡ መልሰው የመጀመሪያው ልብስ አልባሽ፣ ፈጣሪ ‘ራሱ ነው ሲሉኝ፣ መልሼ ተከናነብኩኝ፡፡ አገናኝ አግኝ ፌስቡክ X Pinterest ኢሜይል ሌሎች መተግበሪያዎች አስተያየቶች
ከ “ተደምሬያለው!!” ባሻገር ሴፕቴምበር 12, 2018 ከ “ተደምሬያለው!!” ባሻገር የሴት አያቷና የገጠር ነገር የማይሆንላት ጋደኛዬ መንፈሷ ዝቅ ሲልባትና መነቃቃት ሲያሻት ሁልጊዜም ወደ አያቷና ወደ ገጠር ትኖጣለች፡፡ ጋደኛዬ ልክ እንደ በአሉ ግርማ ሁሉ “ከተማ በድንጋይ ክብር የተሞላ ህይወት አልባ መካን ነው” የሚል ከተማ ጠል የሆነ ደረቅ ፍልስፍና አላት፡፡ ሁሌም ሲመቸኝ እንደማደርገው በዚህኛውም የአዲስ ዓመት መባቻ ከእማሆይ ትርሲት የእውቀት ሁዳድ የአመት ድርጎዬን ለመቀበል ጋደኛዬን ተከትዬ ፍቼ መዳረሻ ላይ ከምትገኘው ከውቧ ቅዬ ከደብረ-ጽጌ ተገኝቻለሁ፡፡ በአንዱ አመሻሽ እኔና እማሆይ ትርሲት ከደጅ ተቀምጠን ስለ ሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታና ስለ መሪያችን ዶ/ር ዐብይ እያወጋን ባለንበት፤ ጋደኛዬ አለም ድንቡሽቡሹን ልጇን ክረምቱን ለአንደኛ ክፍል ለማዘጋጀት በማሰብ ሒሳብ ስታስጠናው አልፎ አልፎ ድምጿ ከቤት ውስጥ ይሰማናል፡፡ ከግማሽ ሰዓት ያህል በኋላ ጓደኛዬ ውብና ትላልቅ አይኖቻ እንደ ክረምት ወንዝ ደፍርሰው ደፍርሶና ቢጫ ፊቷ በርበሬ መስሎ “የማሪያም ጣቷን” ጥፍር በጥርሷ እየበላች አጠገባችን ተቆናጥራ ቁጭ አለች፡፡ አያቷ ሁኔታዋን ከፊቷ ላይ በመረዳት ከኔ ጋር የጀመሩትን ወሬ እንኳን ሳይጨርሱ “አይዞሽ ትምህርት በችኮላና በእልህ አይሆንም፡፡ ደግሞም ልጅ በራሱ መንገድና ፍጥነት ነገሮችን ፈቅዶ መረዳትና መማር ሲችል ነው ጥሩ፡፡ ትምህርት ከየዕለት ኑሮና የህይወት ጉዞ ጋር ካላገናኙት የሚሸመደድ እንጂ የሚረዱት ሊሆን አይችልም፡፡ ልጅን ሲያስተምሩም ሆነ ሲያስጠኑ እኔን እንዳስተማሩኝ ቆርቆሮ የሁለተኛ ደረጃና የዩንቨርሲቲ መምህራን አይነት በቀቀን ሆኖ መቅረብ ትውልድና ሀገርን ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ተማሪዎች ወይም ልጆች የሚማሩት ትምህርት ሙት እንዳይሆንባቸው በመጀመሪያ የትምህርቱን ጽንሰ ... ተጨማሪ ያንብቡ
ውኃ ይሰማል ጉድ በል አበሻ ውኃ ይሰማል አለች ፈረንጅ ሴፕቴምበር 12, 2018 ውኃ ይሰማል ጉድ በል አበሻ ውኃ ይሰማል አለች ፈረንጅ አሸናፊ አበራ ውድ የሸገር ታይምስ ቤተሰቦች እንደምን ሰንብታችኋል? የጥምቀትን በአልን በማሳበብ የጻፍኩትን ” ውኃ ና እግዜር” የሚለውን ጽሁፌን ስደመድም የውኃን ተአምራዊ ተፈጥሮ ለመንገር እንደምመለስ ቃል ገብቼ በነበረው መሰረት ባለቅኔው በአጼ ቴዎድሮስ የምናብ አንደበት ውስጥ “ቃል የእምነት እዳ ነው…”ያለውን አክብሬ እነሆ ተመለስኩ፡፡ ውኃ መሰረታዊ የፊዚክስንም ሆነ የኬሚስትሪን ህግ አይጠብቅም ለምሳሌ ሌሎች ቁሶች ሙቀት ሲነካቸው Heat cause expansion በሚለው የፊዚክስ ህግ መሰረት ሞሎኪውሎቻቸው ይስፋፋሉ ውኃ ግን በተቃራኒው ሙቀት ሲነካው ይኮማተራል ወይም (contract) ያደርጋል በቅዝቃዜ ጊዜ ደግሞ ይስፋፋል፡፡ ከቅዝቃዜ ነጥብ በታች ወይም below freezing point የሌሎች ቁሶች መጠናቸው (density) ሲቀንስ የውኃ ግን ይጨምራል above freezing point ሲሆን መጠኑ (density) ይጨምራል ከቅዝቃዜ ነጥብ በላይ ወይም above freezing point ሲሆን ደግሞ ይቀንሳል፡፡ ውኃ ብቻ የመሬት ስበትን እና ከባቢያዊ ግፊትን ጥሶ በረዣዥም ዛፎች ቅርፊት ውስጥ እያቆራረጠ ሽቅብ እስከ ጫፍ ይወጣል፤ውኃ ብቻ ሲፈልግ ፈሳሽ ሲሻው ጠጣርና ጋዝ በመሆን በተለያ ቅርጽ ይገኛል፡፡ ውኃ ከሌሎች ፈሳሶች በበለጠ ወደ ውስጡ የሚገቡትን ጠጣር ነገሮች በፍጥነት ያሟሟል ሌላም ሌላም፡፡ ውኃ ለምን የተለየ ሆነ የሚለውን ጥያቄ መመለስ የሚችለው እራሱ ውኃ ብቻ ይመስላል ጠያቂው ሳይንስ እንኳን መልሱን አልደረሰበትምና፡፡ የዚህ እንቆቅልሽ ፍቺ ሳይገኝ ተመራማሪዎችን በጥፍር ያቆመ ሌላ ክስተት በደቡብ ምስራክ ኤዠያ ውስጥ ተከሰተ፡፡ ጊዜው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ... ተጨማሪ ያንብቡ
ዶ/ር ዐብይ የህመም ማስታገሻ ወይስ መድሀኒት? ሴፕቴምበር 12, 2018 ዶ/ር ዐብይ የህመም ማስታገሻ ወይስ መድሀኒት? ዶ/ር ዐብይ አህመድ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን “የ ኛ ጠቅላይ ሚንስቴራችን” ሆኖ፤ በደረቅ ወንበር ላይ ሳይሆን በልባችን ዙፋን፣ በጥቂቶችን አፍ ውስጥ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ከነገሰ ዛሬ 138 ቀናት ተቆጠሩ፡፡ በነዚህ ጥቂት ቀናት ውስጥ ግን አጀብ የሚያሰኙና ህልም የሚመስለ ወርቅ ጊዜያትን አብረንው አሳለፍን፡- ዶ/ር ዐብይ እጁን አንስቶ ከማለባት ቀን ጀምሮ “የድሮ ስርአት ናፋቂ እንዳንባል፣ጠባብ ወይም ደግሞ ትምክተኛ የሚባል ታልጋ እንዳይለጠፍብን፣አሊም በግምገማ እንዳንፈረጅ ፈርተን (ለሆድ ለንጀራ) በአደባባይ መጥራት የተውነውን የምዬን ስም አገሪቷ እያሉ አገራችንን ባስረሱን ፊት ፋኖ ሆኖ ኢትዮጽያና ኢትዮጵያዊነትን አመሳጥሮ ጠርቶት ሁላችን በአደባባይ ኢትዮጵያ ብለን መጮህና እውነተኛውን መቀነቷን በግልጽ ከፍ ማድረግ ቻልን፡፡ አብይ በጥቂት ቀናት ውስጥ የጠፋችብንን ኢትዮጵያዊትን ሰጠን፡፡ ከሁሉ በላይ ፍቅርና አንድነታችንን መለሰልን፡፡ የሙያ ነጻነታቸውን “በልማታዊ ጋዜጠኝነት” ስም ተነጥቀው የካድሬ አፍ ሆነው ሲያደነቁሩን የነበሩ የአገር ውስጥ ሚዲያዎችንና ባለሙያዎችን ከእስራታቸው ፈቶልን፤ ዲሽና ኢሳት እያለን እንኳን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን አምነንን መመልከት ጀመርን፡፡ አምሳለ ክርስቶሱ ዐብይ ለአገራቸው ከገዥው ፖርቲ የተለየ ሀሳብ ስላለቸው ብቻ እንደ ይሁዳ ተቆጥረው እንደ ቃየል በየሜዳው ሲሳደዱ የነበሩ የተቃዋሚ ፖርቲ አመራርና አባላቶችን ስማቸውን ቀይሮ የኢትዮጰያ ምርጥ ተፎካካሪ አደረጋቸው፡፡ ኢትዮጵያዊ መሆናችንን ብቻ አክብሮ በግለሰብ ደረጃ የታመመውን እየጎበኝ፣ የተሰደደውን ፈልጐ እያመጣ፣ የታሰረውን እያስፈታ፣ ፍርድ የጐደለበትን ፍትህ እየሰጠ፣ የተበደለውን ይ... ተጨማሪ ያንብቡ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ