ቅዱስ ስካር
ቅዱስ ስካር
እዚህ አንድ ሃይማኖት፣
ሌላ እዚህ ቅዳልኝ፣
ይሄ ነው ‘ሚፈውስ፣
ያኛው ነው ‘ሚያጸድቀኝ፡፡
ምእመኑ በስካር፡-
ያጨበጭባሉ፣
ያሸበሽባሉ፣
ያጎነብሳሉ፣
ይወዛወዛሉ፣
አሜን ብቻ ይላሉ፡፡
ከባንኮኒው ጀርባ፡-
ጥምጣም ያወፈሩ፣
ቀሚስ ያረዘሙ፣
ኮፊታ የደፉ፣
ሙሉ ልብስ ያረጉ፣
አስተናባሪዎች መጠጥ ይቀዳሉ፡፡
ይቀዳሉ፣ይቀዳሉ፣ይቀዳሉ፣ይቀዳሉ፣ይቀዳሉ፣ይቀዳሉ፡፡
በተአምራታቸው ከባዶ ማድጋ ወይን እየቀዱ፣
ህዝቡን ያሰክራሉ፡፡
እኔን የገረመኝ፡-
ገብተው ከሰከሩት፣ እልፍ መጽሀፍት ይዘው ደጅ
የተሰለፉት፣
በእልፍ ይበልጠሉ፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ