ክርስቲያናዊ ስነ-ምግባር


                            ክርስቲያናዊ ስነ-ምግባር  
ጎጆው ልቡ ውስጥ በሚንቀለቀለው የበቀል እሳት ነዳ በቀዝቃዛው ሌሊት ትጨሳለች፡፡
***
ጠበንጃውን አሁንም አሁንም ይወለውላል፣ እጎጆው ግድግዳ ላይ የተንጠለጠለ የዱር ቅል ላይ አነጣጥሮ ባዶ ቃታ ይስባል፣ ጥይቱን አንድ ባንድ እየወለወለ ወደ ቡዋቡዋው ያጎርስና እንደገና አፈናጥሮ አውጥቶ ይወለውለዋል፤ ዳገት እንደሚወጣ ሰው ቁና ቁና ይተነፍሳል፣ እንደ አርበኛ  ከመዲያ ወዲያ እየተንጎማለለ ይፎክራል፣ የወገቡን መቀነት ያጠብቃል ያላላዋል፣ ጠበንጃውን በትከሻው ተሸክሞ ይቆምና ጉልበቱ ላይ አጋድሞት ይቀመጣል፡፡
  ***
ከ 25 አመት በፊት ቤተሰቡ የተቃባውን ደም መልሶ ደም መላሽነቱን ለማረጋገጥ የቀረው የንጋት መምጣት ብቻ ነው፡፡
***
እንቅልፍ ላፍታም እንኳን በአይኑ ሳይኳል ንጋት የጉም ጋቢዋን ደርባ ቀዝቃዛ ፊቷን ገለጠች፡፡ በንዴት አንደጦፈ የጎጆውን በር ከፍቶ ምራቁን መጋኛ ላይ ሲያርከፈክፍ…
***
ምሽቱን በሙሉ አንዳች ሳትተነፍስ አንደ ክረምት ውሻ ጥግ ላይ ተጠቅላ በፍርሀት ስትንቀጠቀጥ ያደረችው ሚሽቱ የሞት ሞቷን አፏን ከፍታ “ባዶ ሆድ ደግም አይደል እስቲ ደረቅ ቂጣ እንካ  አፍህ ላይ አድርግ” ስትል ተሰማች፡፡
 ***
ፊኛን አላልቶ በቁም በሚያሸና የቁጣ አይን ዞሮ ሚሽቱ ላይ አፈጠጠባት፡፡
***
“ዋ! ምን ትላለች ይቺ ሴት፣ ብዬ ብዬ ጦሜን ልግደፍ? ሮብ መሆኑን ዘንግተሸው ነው ወይስ ሴጣን ተጣብቶሽ? በስመአብ በይ አንቺ” ብሎ
***
ግዳዩን ጥሎ ደሙን ሊመልስ በቀል እያገሳ ተፈተለከ፡፡

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ከ “ተደምሬያለው!!” ባሻገር

ውኃ ይሰማል ጉድ በል አበሻ ውኃ ይሰማል አለች ፈረንጅ

ዶ/ር ዐብይ የህመም ማስታገሻ ወይስ መድሀኒት?